Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية  Portuguese
Top banner
Book of the day

መንፈሳዊ_አገልግሎት_መማር_እና_ማስተማር.pdf


  • word cloud

መንፈሳዊ_አገልግሎት_መማር_እና_ማስተማር.pdf
  • Extraction Summary

ተጫሎው ረክ ሺ ሺ ዊሽ በች ኤፊ ኞ ኃይሌ ያፈ በኢኳትዋኛያ ደር የ ሃዋሐዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ዓም ይዘት ቀሩ ምዕራፍ አንድ መንፈሳዊ አገልግሎት ሠ ራስን አለመስበክ እንኳንስ በመንፈሳዊ መድረክ በየትኛውም ስፍራ ስለ ራስ አብዝቶ መናገር ለትዝብት ያጋልጣል የሥነ ልቡና ባለሙያዎች ራስን ከልክ በላይ የማወደስን ፍላጎት ናርሲዝም ብለው የሚጠሩት ሲሆን ከሰብእና ቀውሶች ዩከሀሃ አንዱ ነውም ይላሉ ናርሲስ ፊቱን በውኃ ውስጥ ተመልክቶ ከራሱ ፍቅር የያዘው ነው ይባላል ከሁሉም በላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ሌላ ያመስግንህ አንጂ አፍህ አይደለም ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይደለም ተብሏል ምሳ ራሱን የሚያመሰግን እርሱ ተፈትኖ የሚወጣ አይደለም የሚለው ቃልም ራስን ማወደስ ለፈተና እንደሚያጋልጥ ያስረዳል ቆሮቿ በመንፈሳዊው መድረክም ስለራስ መናገር ራስን መስበክ በመሆኑ የሚገባ አይደለም መምህሩ ለምእመናን ትምህርት የሚሰጥ ወይም አርአያ የሚሆን ነገር በሕይወቱ ቢገጥመው እንኳን ራስን ላለማመስገን ሲል በሦስተኛ ሰው አድርጎ አርቆ ቢናገር ይመረጣል ቅዱስ ጳውሎስ ስለራሱ እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ ብሎ አርቆ መናገሩ የትሕትና መምህር ስለሆነ ነው አረጋዊ መንፈሳዊ የተባለው አባትም በመጽሐፈ መነኮሳት ራሱ ያየውን መንፈሳዊ ምሥጢር የማይዋሸ ሰው ነገረኝ። የአግዚአብሔር ቃል ምግብ ነው በመሆኑም ሥጋዌ ምግብን በመጠን እንደምንመገብ መንፈሳዊ ምግብም መመጠን አለበት አንድ ሰው የቱንም ያህል በላተኛ ቢሆን በዓለም መላውን የምግብ ዓይነት በአንድ ጊዜ ሊመገብ አይችልም ቢሞክረውም ስልት ቀጠና ደዌ ይሆንበታል መንፈሳዊው ትምህርትም እንዲሁ ነው ቤተ ክርስቲያን ብትመጡ ዋጋ የለውም እንዲህ እያደረጋችሁ ከምትጾሙ ባትጾሙ ይሻላል ወዘተ የመሳሰሉ ሃሳቦች ምእመናን እየታገሉም ቢሆን የሚሠሩትን ምግባር እንዲተዉ የሚገፋፋ ነው ሰውን ከኃጢአት ተለይ ለማለት የምትሠራውን መልካም ሥራ ተው ማለት አይገባም ስንት ክፉ ሥራ እየሠራችሁ ሰንበት ብታከብሩ ምን ዋጋ አለው በሚል ንግግር ውስጥ ትልቅ የአመክንዮ ችግር ህፍ አለ ክፉ አትሥሩ ለማለት መልካሚቱን አክብሮ ሰንበት መንቀፍ አይገባም በዚያ ላይ ፌዴጮኢ። ይ ጠቀማል ውስጡ ድረስ ዘልቆ ስበሚወጋውጡ አና እስክ ሐሳቡ ድረስ ከሚመረምደውቡ ቋሉ ይጠቀጣል በፃሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ እንደተባሉ አገልፃሉችን ገልገል ዘወትር በመጎፈላዊ ሕይወት ሰመበርታት በ ታጊጉን በገ ከሚ ፍ ተ ው ፆ አሻ ከ ኞችም አርክ ተካ ብ ነፃ ም ቿ ን ር ጋ ን» መረጠች መባሉ ደዓሞ መማር ከ ሺ ክርር ኤፌ ቾኝ አኔል ኬ ነ አ ሼልዝሕ አገልግልጊ ነው።

  • Cosine Similarity

በወንጌል ሕይወትም የሰው ብርሃነን ነበረች ተብሎ ተጽፏል ሕይወት የተሰኘችው ሥነ ፍጥረት ስትሆን ሕይወት ያላቸውን በማስገኘቷ በመንቀሳቀሷና ምግብ በመሆኗ ጨለማ የተባለ አለማወቅን የምታርቅ የእውቀት ብርፃን ናት ዮሐጸፀ ትር የትምህርት ዓይነትም እንዲሁ የተለያየ ነው የቀለም ትምህርት የተግባረ ፅድ ሙያ ትምህርት የእጅ ሥራ ሙያ መንፈሳዊ ትምህርት አለ በዚህ ምአራፍ ስለ መማር ስናነብ የምናገኘው ሃሳብ ሁሉ መንፈሳዊ ትምህርትን ስለመማር የሚያስረዳ ነው መንፈሳዊ ትምህርት ስንል ደግሞ ቤተ ክርስቲያናችን ከፊደለ ሐዋርያ እስከ ዜማ ከቅኔ እስከ መጻሕፍት ትርጓሜ የምታስተምር ባሕረ ጥበባት እንደመሆኗ በጠቅላላው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ በሆነው ትምህርተ ሃይማኖት ዙሪያ ስለ መማር እንመለከታለን ቤተ ክርስቲያን የቃለ እግዚአብሔር መፍሰሻ ናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዋና ተልዕኮዋ ትምህርተ ወንጌል ነው በዚህም መሠረት ወንጌል ሳታነብብ የምትፈጽመው ምስጢርም ሆነ ሥርዓት የለም ጸሎትዋም ምስጋናዋም በቃለ እግዚአብሔር የተሞላ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምስጢራት የተገነባ ነው የአራቱ ወንንጌሳት ምሳሌ የሆኑት አራቱ አፍላጋት ወንዞች ግዮን ጤግሮስ ኤፍራጥስና ኤፌሶን በምድር ሁሉ ላይ እንደሚፈስሱ ቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ወንጌል የሚፈስስባት ናት በተለይም ው ሓመ መ ናው ው ኣው ትን ቅ ባሎ መንፈሳዊ አገልግሎት ሀገራችን ኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር ምግብ ሆኖ ስለተሰጣት ከጥንት ጀምሮ ስትመገብና ስትመግብ ኖራለች አባቶቻችንም በመጻሕፍት ምስጢራት ውስጥ ሲዋኙ ኖረዋል የኋላ ሰዎች መናፍቃን ተነሥተው ቃሉ ያልተሰማባት አንደሆነች አድርገው እኛ ባንደርስላት ኖሮ ትጎዳ ነበር ሊሉን ይሞክራሉ የመምህርነት መንበርንም ከቤተ ክርስቲያን ቀምተው ለራሳቸው ሊያደርጉ ይጥራሉ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ቀደምት አባቶቻችን በጉባኤ ይከራከሩባቸው የነበሩትን ፃይማኖታዊ ምስጢራት እንደ ተመልካች እንኳን ለመከታተል የሚያስችል የመጽሐፍ ቅዱስ ግንዛቤ የሌላቸው ናቸው ያም ሆነ ይህ በዚህ ምእራፍ የፃይማኖትን ትምህርት ስለመማር እንመለከታለን መማር ሲባልም ሁለቱን መንገዶች የሚያጠቃልል ሲሆን ከቃለ መምህራንና ከቃለ መጻሕፍት መማርን ነው ከቃለ መምህራን መማር መማር ከሁሉ የሚቀድም አገልግሎት ነው። ምአመናን ስለሚያምኑት እምነት እንዲያውቁ ማድረግና በሚያምኑትም ነገር በሥራና በቃል ጸንተው እንዲኖሩ ማድረግ ነው ትምህርቱም ቤተ ክርስቲያን በሠራችው ሥርዓት ወቅትን ጠብቆ ምስጢር ጠንቅቆ የሚሰጥ ነው ለምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት ይበጃል የምትለውን ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች ምእመናንም እንደ ቤተ ጅፒሳኘ ዘቅዱስ ዮሐገስ ስኗዉርት አገልግሎት ወተት ይጠጣሉ ከዚህ ሁሉ እንደምንረዳው ቤተ ክርስቲያን ሕይወት የሚገኝበት የራሷ ትምህርት አላት ዶግማዋንና ቀኖናዋን ትውፊቷን የጠበቀ አስተምህሮም እንዲሁ ይህን የመንፈሳዊ ትምህርት አካሔድና ሥርዓት ካለመረዳት ግን አንዳንድ ጊዜ ሰዎች መንፈሳዊ የሆነን ትምህርት የሜታክቱበት ገዜ አለ ጀርባውን በበላው ስፍራ ብቻ ሲያክኩለት ደስ እንደሚለው ሰው እነርሱ በሚፈልጓቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ ብቻ ትምህርት እንዲሰጣቸውና በሌላው የቤቲ ክርስቲያን ትምህርት ዙሪያ ምንም ነገር ለመስማት የማይፈልጉ አሉ ስለ ዘላለማዊ ሕይወት በምታምን ቤተ ክርስቲያን ስለዚህች ዓለም ብቻ ሲነገር መስማት የሚፈልጉ ስለ ነፍስ ጉዳይ በሚያስጨንቃት ቤተ ክርስቲያን ስለ ሥጋ ብቻ መማር የሚሹ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ የቅዱሳን ተጋድሎና ክብር ሲነገር ጉባኤ ረግጠው የሚወጡ አሉ አንደ ገዛ ምኞታቸው አለ። እንዳልል ብሎ የጸለየው ስለዚህ ነው ምሳኗ ማን በሀብትና ንብረት ብዛት የማይፈታ የአግዚአብሔር ቃል አርዳታ የሚያስፈልገው ብዙ ችግር አለ ስለዚህ ባለጠጎች መማር አለባቸው ሲማሩም ባለጠግነታቸውን ሳያስቡ በትሕትና ይገባል መምህራነ ቤተ ክርስቲያን እነርሱ ሊሆን አንደሚፈልጉት ከድርገው እንዲያስተምሯቸው የሚፈልጉ ከሆነና ከመወደስ በቀር ሌላ ተግሣፅ ለመስማት ፈቃደኛ የማይሆኑ አትንኩኝ ባዮች ከሆኑ መምህራንን እንደ አዝማሪ ወንጌልን እንደመወድስ አድርገዋታል ማለት ነው መንፈሳዊው ትምህርት ግን የሥጋዊ ኑሮ ደረጃን ለይቶ የተላለፈ መልእክት ሳይሆን ለሁሉ የተነገረ ነው ቅዱስ ዳዊት በዓለም የምትኖሩ ሁላችሁ አድምጡ ዝቅተኞችና ከፍተኞች ባለጠጎችና ድሆች በአንድነት በማለት ጥበብን እንዲሰሙ ለሁሉም ሰው የቱንም ያህል ባለጠጋ ቢሆን ባለጠግነቱ ለዚህች ዓለም ብቻ ነው ራቁቱን ወደዚህች ምድር አንደመጣ ራቁቱን ይሄዳል ጌታ ዳግም ሊፈርድ ሲመጣም በአርሱ ፊት ይቆማል በምድር ሳለ መንፈሳ ስንቅን ካልያዘ የሰማዩ ፍርድ ቤት በጉቦና በመማለጃ የሚታለፍ ባለመሆኑ ለዘላለም ጉስቁልና ያዳረጋል ባለጠግነቱም መንፈሳዊ አገልግሎት ሊድነው ይችልም ብበአግዚአብሔርም ቀጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም ተብሎ እንደተጻፈ ሶፎፅ « ምሁራን በሥጋዊ ዘመናዊ ትምህርት በልዩ ልዩ መስኮች የተማሩ ሰዎችም እንደዚሁ የአግዚአብሔርን ቃል መማር ያስፈልጋቸዋል መንፈሳዊው ትምህርት በሥጋዊ ጥበብ ሊመለሱ ለማይችሉ ብዙ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ ነው አንዲሁም በተለያዩ አጋጣሚዎች በዘመናዊ ትምህርት ሰበብ ወደ ተማረው ሰው ኅሊና የገቡ ክፉ አመሰካከቶችና ክህደቶችን ነቅሎ ማውጣት የሚቻለው በመንፈሳዊ ትምህርት ነው የምሁርነት መገሰጫ ይመስል በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በፈጣሪ ሳይ ሊሲዘብቱ የሚሞክሩ የአእምሮ ቅኝ ግዛት እቭበፀ ርዐዕበሸበ በተያዘ አመለካከታቸው ሀገራዊ ባህልንና ትውፊትን የሚያንቋሽሹ የውጪ ሀገር ሰዎችን አመለካከት የሚያወድሱና ለመምሰል የሚጥሩ ሁሉ በሥጋዊ ትምህርት ጠግበው መንፈሳዊ ትምህርትን ያልቀመሱ ናቸው አንዳንድ ጊዜ በሥጋዊ ትምህርት የገፉ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት ሊንቁና ሊያቃልሉ ይችላሉ ትምህርቱ ለእነርሱ እንደማይመጥን የሚያምኑና እነርሱ ባለፉበት የዘመናዊ ትምህርት ሒደት ውስጥ ያላለፈን ሁሉ አንዳይሰሙ ጆሮአቸው የተደፈነ ይኖራሉ በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ስድስተኛ ግለ ታሪክ ውስጥ ኛ ፓትርያርክ መንፈሳዊ አገልግሎች የሚከተለውን ታሪክ አንብቤ ነበር እሂህ አባት በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ወንጌልን በማስተማር ላይ ሳሉ ሁለት ሰዎች በዚያ መንገድ ያልፋሉ አንደኛው ሰው በዘመናዊ ትምህርት ገፍቶ የፕሮፌሰርነት መዐርግ የተሰጠው ነበረ አብሮት የሚሔደው ወዳጄጁ ይህን ፕሮፌሰር ገብተን እንማር። አንደኛ ሰው የዕውቀት ተከፍሎ አለበት የተማረውን ይዘነጋል እንኳን ከሌላ የሰማውን ራሱ ተናገረውን መኣ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚዘነጋ ደካማ ነው ስለዚህ ቃለ እግዚአብሔርን መስማት የዘነጉትን ለማስታወስ ይረዳል በሌላ በኩል የሰሚው ዕውቀትና የመረዳት ችሎታ በየጊዜው እየዳበረ የሚመጣ በመሆኑ ከዚህ ቀደም የሰማውን ትምህርት ደግሞ ሲሰማው ከበፊቱ በተሻለ ደረጃ ሊረዳው ይችላል የእግዚአብሔርን ቃል ቅዱስ ያፅቆብ በመስታወት መመሰሉ ይህንን ያስተምራል ስሰው ዕለት ዕለት ከመስታወት ፊት ይቆማል የየዕለት ጉድፉንም ያወጣል ድሮ አይቼዋለሁ ብሎ መስታወትን አለመጠቀም ፊትን ባላዩት ጉድፍ ይሞላል ቃለ እግዚአብሔርንም ተምሬዋለሁ ብሎ አለመማር ጉዳቱ እንዲህ ነው በፊት ስንማር በቃሉ መስታወት ልናይ የምንችለው በዚያን ወቅት የነበረብንን ጉድፍ ነው ከጊዜ ብዛት የተከማቸብንን የኃጢአት ጉድፍ ለማየት ሁልጊዜም መማር ይኖርብናል በየዘመኑ የሚኖረው መንፈሳዊ ማኅበራዊና ሥነ ልቡናዊ ሁኔታ ተለዋዋጭ ነው የእግዚአብሔር ቃል ግን እስከ ዕለተ ምጽአት ለሚፈጠሩ ሁኔታዎች ሁሉ ምላሽ ያለው ነው ስለዚህ በደህና ጊዜ በደጉ ዘመን ከእነ እገሌ ቃሉን ተምሬያለሁ ብለው የሚያስቡ ሰዎች በክፉው ዘመን ደግመው ቢማሩት ብዙ ነገርን ሊያገናዝቡበት ይችላሉ በቤተ ክርስቲያን በመደበኛነት የሚሰጡ መንፈሳዌ ተከታታይ ትምህርቶችን ከዓመታት በፊት ተምሮ ራስን በቀደምትነት መጥቀስ በአንዳንድ ሰው ዘንድ የተለመደ ነው ከረጅም ጊዜ በፊት ከተማረው ትምህርት ግን ተምሬያለሁ ሽ መንፈሳዊ አገልግሉን ከሚለው ቃል በላይ ምንም በውስጡ የቀረ ነገር አይገኝም ቅዱስ ጳውሎስ ማንም ያወቀ ሊያውቅ እንዲገባው ገና አላወቀም አንዳለው ቃሉን የተማረ ሰው ተዝቆ የማያልቀውን ቃሉን አውቄያለሁ ለማለትም ድፍረት ባልኖረው ነበር በቤተ ክርስቲያን በአገልግሎት በመንፈሳዊ ሹመት በትምህርት ከመቆየት ክብርን ከመልመድ የተነሣ ቃሉን ለመማር የሚቸገሩና መማርን ክብርን አንደማጣት መቁጠርም ተገቢ አይደለም የገማልያል ወንድም መምህር ኒቀዲሞስን በአኩለ ሌሊት አንዲመጣ ካደረጉት ምክንያቶች መምህር ሆኖ ሳለ ገና ይማራል። ሙሽ ሸሸ ድም ምምልድጵምምጮድውጵውምውምው መንፈሳዊ አገልግሎት አብሮ መኖር አለበት የሚያንጸውም ፍቅር ነው ቅዱስ ጴጥሮስ በአውቀትም ራስን መግዛትን ጨምሩ ብሎ እንደተናገረ መንፈሳዊ አውቀት ያለው ሰው ራሱን ከትዕቢትና ድፍረት ለመጠበቅ ራሱን ሊገዛ ይገባዋል ጴጥ እውቀትና ኃጢአት ሲበዛ አይታወቅምና በእግዚአብሔር ቤት በመቆየት ብዙ ለማወቅ ይቻላል ይሁንና በእውቀት የበሰለ ሆኖ በመንፈሳዊ ሕይወት ደካማ መሆን ምንም ጠቀሜታ የለውም ጌታችን ዳግም በግርማ መለኮት በክበበ ትስብእት ሲመጣም የሚጠይቀን የሠራነውን አንጂ የተማርነውን አይደለም ሁሉን የሚማር ብዙ ምስጢርም የሚያውቅ ሰው አለ ነገር ግን ሰውነቱን መጥቀም አይችልም ሲራወጁ እንደተባለ ቃሉን ጠንቅቆ መማር አንጂ በተማሩት መኖር በብዙዎቻችን አይታይም አንድ ሰው ለረዥም ጊዜ በመማሩ ብዙ እውቀትን ሊይዝ ይችላል በተማረው መጠቀም የሚችለው ግን ሕይወቱ ሲኖረው ነው አውቀት በራሱ ከኃጢአት አይጠብቅም የሰው ማንነቱም በሕይወቱ አንጂ በአውቀቱ መመዘን የለበትም ብዙዎች በሚያውቁት ነገር የሚስቱት አውቀት ብቻውን በቂ ስላልሆነ ነው ጌታችን ኃይልን እስክታገኙ ድረስ በኢየሩሳሌም ቆዩ ያላቸው ቅዱሳን ሐዋርያቱ በሦስት ዓመት ትምህርት በቂ እውቀት የጨበጡ ቢሆኑም በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊያን ሳይሆኑ በአውቀታቸው ብቻ ራሳቸውንም ሌላውንም ለመጥቀም ስለማይችሉ ነው ከመማር ብዛትም አንድ አባት እንደተናገሩት ከአማኝነት ወደ ሊቅነት መቀየር ይመጣል በምንማረው ትምህርትም ራሳችንን ዴሎ ር መንፈሳዊ አገልግሎት መገሠፅና መውቀስ ትተን የንግግር አወራረዱን የቃላት አጣጣሉን የትምህርት አወቃቀሩን ብቻ የምንመለክትበት ጊዜ አለ ይህ አግዚአብሔርን የሚያስደስተው አይደለም አንድ አባት ልጁን ሲመክር ልጁ የአባቱን አነጋገር ቃላት አጣጣል እያዳነቀ ቢናገርለት የሚለውን ግን ባይሰማው ደስ እንደማይለው እኛም ቃሉን ስንሰማ መልእክቱን ትተን የቃላት አወራረዱን ማድነቃችን አምላክ ደስ አይሰኝበትም የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የሆኑት ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ በአንድ ወቅት የተወሳሰበ ምስጢራዊ ዐረፍተ ነገር ከአንድ መንፈሳዊ መጽሐፍ ሲያነብቡ ሊቃውንት ስለዚህ ቃል ትርጉም ሲወዛገቡ ስንት የዋሃን ምእመናን ወደ መንግሥተ ሰማያት ገብተው ይሆን። በእነርሱ እጅ ያመናችሁ አገልጋዮች ናቸው ለእያንዳንዳቸውም ጌታ እንደሰጣቸው ያገለግላሉ ብሏል ፅቆሮ ፁይፎ በእነርሱ እጅ ያመናችሁ አገልጋዮች ናችሁ የሚለው አንድ ነገር ያስታውሳል አንድ ሰው ወደ መንፈሳዊ ሕይወት የገባው በአንድ መምህር ስብከት ተመስጦ ሊሆን ይችላል ይህ የእግዚአብሔር አሠራር ነው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው በአጵሎስ አጅ ወይም በጳውሎስ እጅ ያመነ ሰው በአርሱ እጅ አምጌፄኔአለሁ ብሎ የአጵሎስ ነኝ ወይም የጳውሎስ ነኝ ማለት አይገባውም ጳውሎስና አጵሎስ በአጃቸው እንዲያምን ያደረጉት እነርሱን ብቻ በሔዱበት እንዲከተል ለሌላው ጆሮ እንዳይሰጥ ስለእነርሱ ጥብቅና እንዲቆም የእነርሱ ነኝ እንዲል አይደለም እነርሱ ያስተማሩት ወደ አግዚአብሔር ቤት ጠልቆ እንዲገባ ነው ለምሳሌ አንድ ሰው ወደ አንድ ትልቅ ከተማ በአንድ በር አማካይነት ዘልቆ ቢገባ ከተማይቱን ዞሮ መጎብኘት ትቶ የገባበትን በር ሲያደንቅና ከእርሱ አልለይም ሲል አይኖርም በአንድ መምህር ምክንያት ወደ መንፈሳዊነት ተጠርቼያለሁና እርሱን ብቻ ልከተል ማለትም እንዲሁ ነው ለአንድ መምህር የሚሰጥ የተጋነነ አድናቆት ብዙ የጎንዮሽ ጉዳት አለው አንደኛ መምህሩ ሰው መሆኑን ወደ መዘንጋትና ስኀኅተትም ቢፈጽም አርአያ ማድረግ ይመጣል አያድርገውና ከሃይማኖት ቢወጣ ደግሞ ተከትዬ ልውጣ ማለትም ይከተላል ሌሎች መምህራንንም ለመስማት ፈቃደኛ አለመሆንና መጥላትም ይመጣል የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተማሪዎች ያደረጉት ይህንን ነበር ጌታችን በትሕትና በዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አይተውት ነበር ይሁንና የጌታ ተከታዮች ሲበዙ የዮሐንስ ተከታዮች ሲያንሱ ተመልክተው ለመምህራቸው ተቆርቁረው መምህር ሆይ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው አንተም በየመሰከርህለት እርሱ ደግሞ ያጠምቃል ሁሉም ወደ እርሱ ይመጣሉ ብለው በቃለ ጸብእ በጠብ አነጋገር ስለጌታ ለዮሐንስ ነገሩት አርሱ ግን መንፈሳዊ መምህር በመሆኑ ከሰማይ መንፈሳዊ አገልግሎት ካልተሰጠው በቀር ሰው አንዳች ሊቀበል አይቸልም በማለት እውቀት ኖሮት ለማስተማር አግዚአብሔር ካልሰጠው በቀር ማንም እንደማይችል ጌታን ለመከተልም መቻል ራሱ ከአግዚአብሔር ካልተሰጠ በቀር የሜቻል ነገር አንዳልሆነ ነገራቸው አኬ የአርሱ መንገድ ጠራጊ ነኝ ምእመናን ወደ አርሱ ሲፄዱ ሚዜ በሙ ሽቭራና ሙሽሪት አንድነት እንደሚደሰት ደስ ይለኛል አላቸው ዮሐጀ ጌታችን መምህር አየመረጡ የሚቀማጠሉ አይሁድን ክፉና አመንዝራ ብሏቸዋል አመንዝራ ሴት ነገሩ አንድ ዓይነት ሆኖ ሳለ ዕለት ዕለት ወንድ ሊለወጥላት አንደምትወድ ቤተ አይሁድም ዕለት ፅለት ትምህርት ቢለወጥላቸው ይወዳሉ ትምህርቱ ቢለወጥም ግን አነርሱ አልተለወጡም ማቴወሀ መምህራንን ስለ በጎ አገልግሎታቸው ማመስገንና ስለ አነርሱም መጸለይ የሚገባ ክርስቲያናዊ ተግባር ነው ይህ ግን መምህሩ በራሱ ኃይልና እውቀት ብቻ የሚያገለግል አስኪመስልና ሰው መሆኑን አስከመርሳት ድረስ መድረስ የለበትም ስለዚህ ጥሩ መምህር ሲገጥም ለመከሩ ብዙ ሠራኞችን መምህራንን የሰጠ የመከሩ ባለቤትን እግዚአብሔር መምህራንን ባያስቀርልን ኖሮ ሰዶምና ገሞራ የሚያስተምራቸው አጥተው አንደጠፉ በጠፋን ነበር። የእግዚአብሔርን ቃል ስዎች ስለ ብዙ ምክንያት ይማራሉ ስለ ሕይወቱ መቃናት ስለ ምግባሩ መስተካከል ሲል የሚማር አለ ስለሚያምነው ሃይማኖት ለመጠንቀቅና ለማወቅ የሚማር አለ ይህ መልካም ነው አምነት ከመስማት ነው መስማትም ክእግዚአብሔር ቃል ነው ተብሎ እንደተነገረ ፅውቀት የበለጠ በፃይማኖት ለመጽናት ይረዳል መናፍቃንና አረማዊያን ሲያስጨንቁት የእነርሱን አፍ ለማስዘጋት ሲል የሚማርም አለ በባደኞቹ መካከል ሁሉን አዋቂ ነኝ ለማለትና ማብራሪያ ሰጪ ለመሆን የሚማር አለ እንደ አይሁድ መምህሩን ለመገምገምና እንከን ለማውጣት የሚማር አለ ሁለገብ ሰው ሆኖ ለመታየት መንፈሳዊ ትምህርትን እንደሌሎች ሙያዎች የሚማር አለ ቤተ ክርስቲያንን ለመቃወምና ለመክራክር ብሎ የሚማር አለ መንፈሳዊ ትምህርትን በመንፈሳዊ ሥፍራ የሥራ ዕድል ለማግኘት ብሎ የሚማር ሰው ይኖራል በቤተ ክርስቲያን የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ለመሆን ፈቃደኛ መሆንና እንደ አሮን በእግዚአብሔር ቤት ባለርስት ሆኖ መተዳደርን መምረጥ መልካም ነው ይሁንና በተማረው መንፈሳዊ ትምህርት መቀጠርንና ደመወዝ ማግኘትን የመጨረሻ ግብ አድርጎ ከወሰደው ትምህርቱ ለሕይወት አይሆነውም ስለዚህ በመንፈሳዊ ትምህርት ገፍቶ በቤተ ክርስቲያን በቋሚነት ማገልገል የሚሻ ሰው የተማረውን መንፈሳዌ ትምህርት ብ መንፈባሳዊ አገልግሎት ከተራ የጉልበትና የሒሳብ ሥራ ሙያ ለይቶ የሚያይበት መንፈሳዊ ዓይን ሊኖረው ይገባል ከቃለ መጻሕፍት መማር በዓለም ላይ በዓይነታቸውና በሚያስተላልፉት ጭብጥ ልዩ ልዩ የሆኑ መጻሕፍት አሉ የረከሱና ሊነኩ የማይገባቸው መጻሕፍት በጥንቃቄ መነበብ የሚገባቸው ተራ መጻሕፍት አሉ በዚህ ንዑስ ርአስ ከቃለ መጻሕፍት መማር ስንል መንፈሳዊያት መጻሕፍትን የሚመሰለከት ነው ክርስቲያኖች አሥራው መጻሕፍት ተብለው ከሚጠሩት መጽሐፍ ቅዱስ በምንለው መድበል ከተካተቱት መጻሕፍት ጀምሮ እስከ አዋልድ መጻሕፍት ድረስ ያነብባል ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ በመጻሕፍተ መነኮሳት ከጾም ከጸሎት ከስግደትና ከምጽዋት ጋር አብሮ እንደ ትሩፋት የተጠቀሰ መንፈሳዊ ሥራ ነው መጻሕፍትን መመልከት ከአውቀት ባሻገር በሃይማኖትና በምግባር ለመጠንከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል የአግዚአብሔርን ትአዛዝ ዐስብ መጻሕፍቱንም ሁልጊዜ አንብብ አርሱም ልቡናህን ያጸናዋል ጥበብንም ትወዳት ዘንድ ይሰጥፃል ሲራሯሠወጃ ተብሎ እንደተነገረ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ በሃይማኖት ያጸናል መጻሕፍትን መመልክትም እግዚአብሔርን ወደማድነቅና ወደ ማክበር ይመራል አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቅ እንደተናገረውም በጸሎት ጊዜ ምኑናት መዛሕፍት የተናቁ መዛሕዬትየትምህርት መርጃ የታልክ መዘተ ቅዱሳት መዘሕፍት ስሥራው ዘዘሕዬትመጽሐፍ ቅትዱስ ስና ስቸሰድ ዘጸሕፍዬትን ርኩሳት ዘዉጸሕፍት የጥኀቅጓ የስስማት የኑፋዌቄና ከህደት መጻሕፍት መንፈሳዊ አገልግሎት ሩሩ አግዚአብሔርን እኛ የምናነጋግረው ሲሆን መጻሕፍትን በምናነብበት ጊዜ ግን እግዚአብሔር ያነጋግረናል እግዚአብሔር ለሕዝቡ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል ተብሎ እንደተጻፈ መዝ ቿጂዕሄ ጌታችን መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ እንዳለ መጻሕፍትን አለማወቅ ለስኅተት ይዳርሠጋል የቅዱሳት መጻሕፍትን ጠቀሜታ የተረዳችው ቤተ ክርስቲያናችን በብዙ መንገድ ስለ መጻሕፍት ክብር ታስተምረናለች የኅትመት መገናኛ እንዲህ ባልተስፋፋበት ዘመንም ብርዕ ቀርጻ ብራና ዳምጣ ቀለም በጥብጣ መጻሕፍትን በዕደ ሊቃውንት አያዘጋደጆች ለዚህ ትውልድ አድርሳለች ቅዱሳት መጻሕፍትንም ሸልማና አክብራ ታነባለች ለልጆቿም ታሳልማለች መጻሕፍትንም በማኅበርና በግል እንዲያነብቡ ለምእመናን ሥርዓትን ሠርታለች በቤተ ክርስቲያናችን መደበኛ ትምህርት መጻሕፍትን ከመጻፍ እስከ መደጎስ ራሱን የቻለ ሙያ ያለ ሲሆን ይህም ቤተ ክርስቲያናችን ምን ያህል የመጻሕፍትን ጥቅም እንደምታውቅ ያስረዳል መጻሕፍትን ማንበብ በማንኛውም መስክ ቀዳሚ የሚያደርግ ነው በዓለም ላይ በየመስኩ የተሳካላቸው ሰዎች ብዙኃኑ አንባቢያን ነበሩ በመንፈሳዊው ሕይወትም መጻሕፍትን መመልክት ለአውቀትም ለሕይወትም የሚረዳ ልምድ ነው መንፈሳዊያት መጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፉ እንደመሆናቸው ሕይወትን የሚመረምሩ የሚያነብባቸውንም የሚያነብቡ ናቸው ሽ መንፈሳዊ አገልግሎት መንፈ ሳዊያት መጻሕፍትን ምሥጢር ገላጭ የሆነ አግዚአብሔርን አስቀድሞ በመለመን ማንበብ ይገባል እንደ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባም የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት መረዳት ይቻለኛል በማለት መጻሕፍትን ከማንበብ ጋር መምህራንን መጠየቅ ያስፈልጋል የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ። ቤተ ክርስቲያናችን ባሕረ ጥበባት አንደመሆኗ የትምህርቷን ዘርፍ እንኳን ለመዘርዘር ሌላ ትምህርት የሚሻ መሆኑ ግልጥ ነው ይሁንና ሰፊውን ትምህርተ ቤተ ክርስቲያን ለመዝለቅ የዕድሜ ገደብ የዓቅም ማነስ ቢኖርም አንኳን መሠረታዊ የሆኑትን የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማ ቀኖናና ትውፊት ማወቅ አንኳን ለማስተማር ክርስቲያን ለመሰኘትም ወሳኝ ነው ሊቃውንት የሚያምነውን አምነት ምንነት ሳያውቅ የሚኖርን ሰው የጌታውን ቤት በማያውቅ ከቤት አንስሳት በሚያንስ በዱር አውሬ ይመስሉታል የዱር አራዊት ከቤት እንስሳት የሚያንሱት ጌታቸውን ባለማወቃቸው ቤቱን ባለመጠበቃቸው አንደሆነ ሁሉ ሃይማኖትን ያልተማሩትም አምላካቸውን ባለማወቃቸው ትአዛዙንም ባለመጠበቃቸው ከተማሩት ያንሳሉ ለእመ ኢተምህሩ ሃይማኖተ ሥሉስ ቅዱስ ወኢይበሉ ክርስቲያን ንሕነ ወንድኅን ቦቱ አኮ ሰብእ አላ አራዊት ዘገዳም አሙንቱ በሦስቱ ቅዱስ ማመንን ካልተማሩ ክርስቲያን ነን እንድንበታለን አይበሉ ሰው አይደሉም የዱር አራዊት ናቸው እንጂ እንዲል ድርሳነ ሰንበት ስለዚህም መሠረታዊውን ትምህርተ ሃይማኖት መማር ለሁሉም ከዚያም አልፎ በጥልቀት መማር ደግሞ ለመምህራን ይገባል አንድ መምህር ከሚያስተምራቸው ምአመናን በላይ ካልተማረ መምህር የሚያሰኘው ምንም ምክንያት አይኖርም ምክንያቱም መምህር ማለት የማያውቁትን የሚያሳውቅ የሚመክር የሚገሥፅ ማለት ነውናመንፈሳዊ ትምህርት እንደቃለ ተውኔት ተጠንቶና ተሽምድዶ የሚቀርብ ሳይሆን ከተማረ ልቡና መዝገብ የሚወጣ ነው መምህሩ አስቀድሞ የሚያስተምረውን ሊያውቀውና ሊረዳው ያስፈልጋል የሚያስተምረውንም ካላወቀና ካልጠነቀቀ ሌሎችም ከአርሱ ተምረው ሊያውቁ አይችሉም አስመ ውእቱ ለእመ ኮነ የአምር ዘይብሎ እሉኒ ይሰምዕዎ የአምሩ ዘይብሎሙ አርሱ የሚያስተምረውን ካወቀ የሚሰሙትም የሚላቸውን ያውቃሉና ተብሎ አንደተጻፈፍትሐ ነገሥት ባለንበት ዘመን በማስተማር አገልግሎት ለመሠማራት የሚያበቃ ጥልቅ መንፈሳዊ እውቀት አለ ለማለት ያስቸግሣራል ቅዱስ ዳዊት ፈለገ እግዚአብሔር ምሉዕ ማያተ የእግዚአብሔር ወንዝ ውዣችን የተሞላ ነው አንዳለ በቃሉ ውኃ የተሞሉ የቀደሙት መምህራን አውቀትና ሕይወት አሁን በስፋት አለ ለማለት አንደፍርም መዝ ካነበቡትና ከተማሩት በላይ የኖሩትን ያስተምሩ የነበሩትን የቀደምት አበው ትምህርት ምንም ዓይነት ስልጠናና ትምህርት ሳይወስዱ ምስክር ወረቀት ሳይቀበሉ አልጆችሽ በእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ እንዲል እርሱ እግዚአብሔር አሰልጥኖአቸው አርሱም ምስክር ሆኗቸው ያለማወቅን ጽልመት በትምህርታቸው ብርፃን ያራቁ ቅዱሳን መምህራን መንፈሳዊ ብቃት በዚህ ዘመን አለ ለማለት አንነሣም ይሁንና በአነርሱ ፈንታ ልጆች አንደሚወለዱም ንግርት አለና በአበው ደረጃም ባይሆን ከአባቶቻቸው የሰሙትን የሚሜናገሩ ዴዴ መንፈሳዊ አገልግሎት ያልተነገራቸውን ደግሞ ኢሰማዕነ ወኢርዒነ ወኢነገሩነ አበዊነ አልሰማንም አላየንም አባቶቻችንም አልነገሩንም» አያሉ የሚያስረዱ ልጆች መኖራቸው አልቀረም የሚገባውን ያህልም ባይሆን መሠረታዊውን ትምህርተ ሃይማኖት የሚያውቁ ደቀመዛሙርት ተማሪዎች ልጆቿን ቤተ ክርሰቲያን ለስብከተ ወንጌል ታሰማራለች በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓተ ትምህርት እየተማሩ ማስተማር የተለመደ ነው ለምሳሌ ንባብ የተማረው ያልተማረውን እያስተማረ አሱ ዜማ አንደሚማር ክርስቲያን ልጆች የተማሩትን አያስተማሩ ያልተማሩትን የቤተ አግዚአብሔርም በተሰጣቸው ትንሽ መማራቸው ተገቢ ነው መክሊት ማትረፋቸውን ተመልክቶ የበለጠውን ጸጋ ያድላቸዋል ችግር የሚፈጠረው ግን በማስተማሩ ሰጥሞ የመምህርነት ትዕቢት ተሰምቶት መማሩን በሚተው ላይ ነው አንዲህ ሲያደርግ መማር ስላቀመ ትምህርቱም የዚያኑ ያህል አየሳሳ ይመጣና ቀድሞ የተማረውን ሲጨርስ የማይጠቅም ነገር ወደመናገር ያመራል ጌታችን መምህር ኒቆዲሞስን አንተ መምህር ስትሆን ይህንን አታውቅምን። በአምነት ማስተማር በሥጋዊ የቀለም ትምህርት በመምህርነት ላይ ያሉ ሰዎች የሚያስተምሩት ሙሉ በሙሉ የሚያምነበትን ነገር ላይሆን ይችላል ምክንያቱም ሥርዓተ ትምህርቱ የሚቀረጸው በዘመኑ ከተደረሰበት የአውቀት ደረጃ አንጻር ስለሆነ ነው አስተማሪውም ማስተማር ግዴታውና ሥራው እንደመሆኑ ያሳመነበትንም ነገር ሊያስተምር ይችላል የማስተማር ሥራውን በሚገባ አስከተወጣም ድረስ በምታስተምረው ነገር የግድ ማመን አለብህ ብሉም የሚያስገድደው አይኖርም መንፈሳዊ ትምህርት ላይ ግን ይህ ጽንሰ ሣሃሳብ አይሠራም በመጀመሪያ ደረጃ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ላይ እምነት የሌለው ሰው እንኳን መምህርነቱን ምአመንነቱንም አጥቷል ቁጥሩም ከመናፍቃን ወገን ነው እንዲሁም የራሴን አመለካከት በውስጤ ይዝ ያላመንሁበትን አስተምራለሁ ቢል እንኳን አንደ አርዮስ ይቀሠፋል የማስተማር አገልግሎትም የፈቃድ እንጂ የግድ አይደለም ያላመነበትን ነገር ደግፎ መናገርን መጽሐፍ ቅዱስም አይደግፈውም ክፋት በልቡ ሳለ ፍቅርን የሚናገር ከንፈር በብር ዝገት እንደተለበጠ የሸክላ ዕቃ ነው ይላል ምሳጄ በውስጡ እምነት የሌለው መምህር እንዴት ባላመነበት ነገር ሌላውን ሊያሳምን ይችላልን ትምህርቱም ከአምነት ጋር ባለመሆኑ ሳይዋጥለት እየተናነቀው የሚያስተምረው ትምህርት ሰሚውን ት የ ሎች ከቴ ዲ ብ ፒቲ ያጠራጥራል መጽሐፍ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና በማለት በአፍ ከመመስከር በፊት በልብ ማመን እንደሚያስፈልግና እንድሚያጸድቅም ይናገራል ሮሜል ጌታውን አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ስለ ጌታ መልካም ነገርን የተናገረና በፍቅር ምልክት በመሳም የቀረበው ቢሆንም በልቡ ስለካደው አልተጠቀመም በማያምንበት ነገር የሚያስተምርም መምህር አንደዚሁ አይጠቀምም ቅዱስ ዳዊት አመንኩ በዘነበብኩ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ በማለት የሚናገሩትን ስለማመን አስረድቷል መዝል ንዋይ ኅሩይ ምርጥ ዕቃ የተባለ ቅዱስ ጳውሎስ ይህን የዳዊት ቃል ጠቅሶ ነገር ግን አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን እኛ ደግሞ አናምናለን ስለዚህም እንናገራለን ብሏል ቀሮቭ ቅዱሳን ሐዋርያት ትምህርታቸው ከአምነት ጋር ስለነበር የሚሰሙት ሰዎችንም ይለውጥና ምንተ ንግበር ምን እናድርግ። ያሰኝ ነበር ቅዱስ ዳዊት አእግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም እንዳለ አንድ መምህር ሰዎች የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዲቀምሱ የመጋበዝ ሐላፊነት አለበት መዝቋር ነገር ግን አስቀድሞ አርሱ ያልቀመሰውን ቅመሱ ማለት አይችልም ምግብንም ቢሆን ይጣፍጣልና ኑ ቅመሱ ለማለት አስቀድሞ መቅመስ ያስፈልጋል አንድ መምህር በእምነት ያላጣጣመውን ነገር ቢያስተምር ትምህርቱ መረጃን መስጠት እንጂ ምስክርነት መ መንፈሳዊ አገልግሎት አይሆንም ከውስጣዊ ፍቅርና ከልብ ያልመነጨ መልእክትም የሌላውን ልብ ሊማርክና ሊመልስ አይችልም ያለ እምነት የሚሰጥ ትምህርት ዕውቀትን ማስተላለፍ ብቻ እንጂ መንፈሳዊ አገልግሎት ሊባልም አይችልም ባላመኑበት ነገር ማስተማር መገለጫዎቹ ብዙ ናቸው የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት የሚመነጨው ከመጽሐፍ ቅዱስና የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያዎች ከሆኑ ከአዋልድ መጻሕፍትና ከትውፊት ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ ነው ለመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተዘጋጁ የትርጓሜ መጻሕፍት አሉ እነዚህን ሊያካትት የማይፈቅድ መምህር ኦርቶዶክሳዊ ሰባኪ ነው ለማለት ያስቸግራል ቤተ ክርስቲያናችን ሰፍራ ቆጥራ በቀኖና የለየቻቸውና የምትቀበላቸው ሰማኒያ አንድ መጻሕፍት አሏት እነዚህን መጻሕፍት በሙሉ እምነት ተጠቅሞ ማስተማር የመምህራን ሥራ ነው በመጻሕፍቱ አምናለሁ እያለ ሊጠቅሳቸው የማይፈልግ መምህር በቃሉም ባይሆን በተግባር እአየካዳቸው ነው ከመጽሐፍ ቅዱስ የተገኙ አዋልድ መጻሐፍትንም መጠቀም ይገባል ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የአግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማጽናት በጽድቅም ላለው ምክር ሁሉ ይጠቅማል ብሎታል ይህም አዋልድ መጻሕፍት ለትምህርት ለተግሣጽ አንደሚጠቅሙ የሚያስረዳ ነው ጢሞ አመ የቅዱሳን ገድላትና ተአምራት እየጠላ ክብረ ቅዱሳንን አምናለሁ ማለትም አይቻልም አባ ጽጌ ድንግል ለእመቤታችን በደረሰው ምስጋናው እወድሻለሁ የሚል ክርስቲያናዊውን ተአምርሽን የማይወድ አይሁዳዊና የሐሰተኛው እስጢፋ የወጣ ነው አንጂ ብሏል ዘሰይብል አፈቅረኪ ወኢያፈቅር ተአምረኪ ክርስቲያናዊ ኢ ክርስቱን ውእቱ ዳዕሙ አይሁዳዊ ወሠርፀ እስጢፋ ሐሳዊ እንዲል ማኅሌተ ጽጌ ተብሎ ይታመናል አባቶች ይላሉ ምናልባት የሚሉ ቃላትን የሚጠቀም መምህር ከእምነት ጋር እያስተማረ ነው ማለት አይቻልም በሕይወቱ የተረዳውን የሚያስተምር መምህር ግን ሌሎችን እርሱ ያየውን እንዲያዩ ሊስባቸውና ሊያጓጓቸው ይችላል መንፈሳዊ ትምህርትን ለማስተማር እውቀት ብቻ አይበቃም ቅዱሳን ሐዋርያት የሰማነውን እንናገራለን ያየነውን እንመሰከራለን። አገልግሎት ምስጢር እየነገረም ግራ አያጋባቸውም ነበር የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም በማለት ተናግሮአል ዮሐጅ ትምህርቱንም ሰዎች ከሚኖሩበት የአኗኗር ዘዬና ከዕለት ተፅለት ተግባራቸው ጋር አስተሳስሮ ያስተምራቸው ነበር ለገበሬው በዘርዕና በአትክልት ሥፍራ ለእረኛው በእንስሳት ለሴቶች በእርሾ ለነጋዴው በገንዘብ እንዲሁም ሁሉም ሰው ሊረዳቸው በሚችሉ ተፈጥሮአዊ እውነታዎች ላይ ምሳሌን እየመሰለ ማስተማሩ ለሰው በሚረዳው ለማስተማርና ትምህርቱን ከሰማዕያኑ ዓቅም ጋር ለማጣጣም ነበር ቅዱስ ጳውሎስም በሽማግሌዎች መካከል ግን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን ማለቱ የሰማዕያኑን ዐቅም እንደሚገመግም ያሳያል ፅቆሮዌ ነገር አለማብዛት አበው ብዙ ቢያወጉ ይዘነጉ ብዙ ቢተቹ ይሰለቹ እንዲሉ መምህሩ ነገር አብዝቶ ባስተማረ ቁጥር ከምን ተነሥቶ ከዚህ ደረሰ ይባላል ነገር ማብዛት ዝንጋዔን መዘንጋትን ያስከትላል መጽሐፍ ግብር ዘአልቦ ምጣኔ ገዓር ውእቱ ወለገዓርኒ ይተልዎ ዝንጋዔ ይላል ልክ የሌለው ሥራ ድካም ነው ድካምንም መዘንጋት ይከተለዋል» ማለት ነው አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም የአመቤታችንን ቅዳሴዋን ሲጀምር ኃዖ ጎፖሮ በቃፅ ፄ ለ ሳለድሮ መዘንጋት ባለበት በማብዛት አይደለም በማሳነስ ነው እንጂ በማለት ነው የትምህርት መርዘም መዘንጋትን የሚያመጣው በሁለቱም ወገን ን ነው መምህሩ ነገር በማስረዘሙ የተነሣበትን ጭብጥ እንዲዘነጋ ያደርገዋል በዚህ መንገድ ትምህርቱ ቅርጽ የሌለው እንዳይሆን ያደርገዋል በትኩረት የትምህርቱን አወራረድ የሚከታተል ተማሪ ካለም መማሩን ትቶ የመምህሩን ዝንጉነት ይታዘባል ቅዱስ ጳውሎስ ጣዕመ ትምህርቱ የሚያስደንቅ መምህር ነበር ይህ መምህር ግን አማረልኝ ብሎ ነገር ማብዛት አንደማይገባና ትምህርትን በጊዜ መመጠን አንደሚያስፈልግ ሲያስረዳ ሁሉን አንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል ብሷል ዕብፅ ወ በአርግጥም መምህር በአንድ ቀን የሚያውቀውን ሁሉ ተናግሮ ሊፈጽም አይችልም በርአሰ ጉዳይም አንድ ነገር ላይ ብቻ ማስተማር ይገባል እንጂ ሁሉንም ነገር በአንድ ቀን ተናግሮ መፈጸም አይቻልም ቅዱስ ጳውሎስ በቃሉ ይህን ከመናገሩ አስቀድሞ በተግባር ትምህርት ማስረዘም ሌላ ውጤት ሲኖረውም አንደሚችል ከታሪኩ መማር ይቻላል ይህ ሐዋርያ ጢሮአዳ በምትባል ሀገር ለሰባት ቀናት ከሰነበተ በኋላ በማግሥቱ ሊሔድ ባሰበበት በዕለተ ሰንበት ምሽት እስከ አኩለ ሌሊት ድረስ ነገሩን አስረዝሞ ነበር የተሰበሰቡበት ሰገነት እአጆግ መብራት የበራበትና ሙቀት ያለበት ነበረ አውጤኪስ የሚባል ወጣት በመስኮት ላይ ተቀምጦ ትምህርቱን ሲሰማ ነበር ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ አንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ ሞቶም አነጮት ቅዱስ ጳውሎስ በላዩ ወድቆ አቅፎ ያዘው አነርሱንም ሃፍሱ አለችና አትደንግጡ አላቸው እስኪነጋም ድረስ መንፈሳዊ አገልግሎት ፒ ጐ ሎ አስተማራቸው አውጤኪስ ከፎቅ ሲወድቅ በወቅቱ ያስተምር የነበረው ሀብተ ፈውስ የተሰጠው ሙታንን በጸሎቱ የማስነሣት ጸጋ የተሰጠው ቅዱስ ጳውሎስ መሆኑ በጀ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ በቅድስና ሆኖ የሚያስተምረው የቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት በመርዘሙ ብቻ ይህን ካስከተለ የላመ የጣመ እየተበላ የሚሰጠው ትምህርትማ ምንኛ መመጠን ይገባው ይሆን። በሌላ በኩል አለመጠን የሚረዝም ትምህርት ምእመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ወንጌልን ለመስማት እንዳይመጡ የበኩሉን አሉታዊ ድርሻ ያበረክታል በተለይ ለመንፈሳዊ ትምህርት አንግዶች የሆኑ ምእመናን በኅሊናቸው መንፈሳዊ ትምህርትን ተደምሮ ቶሎ የማያልቅ አድርገው እንዲያስቡና ሌላ ጊዜ ለትምህርት እግራቸውን እንዳያነሠ ምክንያት ሊሆን ይችላል ከራሳቸውም አልፈው ለሌሎች ሰዎች አእነሱ ከጀመሩ አይጨርሱም ብለው ሊያውጁ ይችላሉ ስለዚህ መምህሩ ምእመናን እስኪንገሽገሹ ድረስ መናገር የለበትም በየመድረኩ እኔ አንኳን ብዙ የምለው የለኝም በሚል መግቢያ ብዙ ማለት አየተለመደ መምጣቱ ብዙዎችን መንፈሳዊ መድረክን መቋጫ አንደሌለው አድርገው እንዲደመድሙ ምክንያት ሆኗል ምናልባት መምህሩ ብዙ በመናገሩ የምእመናንን ልቡና መመለስ አንደሚችል ገምቶ ከሆነም ተሳስቷል ፍሬ ያለው መንፈሳዊ ትምህርት ለብዙ ሰዓት ከሚነገር ሥጋዊ ንግግር የበለጠ ኃይል አለው ጌታችን ሐዋርያው ስምዖን ቀነናዊን ናትናኤልን ሠከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ በሚል አረፍተ ነገር ብቻ ሁሉን ትቶ መ መመመ መ መመ ማሎ ቺነ መንፈሳዊ አገልግሎት እ ንዲከተለው ያደረገው ብዙ ስለተናገረ ሳይሆን ሕይወቱን የሚዳስስ ኃይል ያለው አጭር ቃል በመናገሩ ነው። ቢሰጥ ተገቢ በሆነበት ወቅት ያልተሰጠ የትምህርት ርእሰ ተዳይን አስታውሶ በሌላ ጊዜ የሚያነሣው አይኖርምና በዓመታዊ ክብረ በዓላት ላይ ከዋዜማው ጀምሮ ወቅቱን የሚመለከት ትምህርተ ወንጌልን መስጠት ከመምህራን ይጠበቃል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወቅታዊ ትምህርትን እያስቀረ የመጣ አንድ ባህል አለ ለምሳሌ በአንድ በዓለ ንግሥ ዋዜማ የሚያስምር መምህር ነገ ይማሩታል ብሎ ስለ በዓሉ ከመናገር ይልቅ በሌላ ርእሰ ጉዳይ ያስተምራል በበዓለ ንግሥ ላይ የሚያስተምረው መምህር ደግሞ ከሰዓቱ ጥበት አንጻር ወይም ከዋዜማው ጀምሮ የተማሩት ነው ማታም በሠርክ ጉባኤ በሰፊው ይማሩታል ብሎ በጥልቀት አያስተምርም በሠርክ ጉባኤ ላይ የሚቆመው መምህር ደግሞ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ጠዋት ድረስ ሲማሩት የከረሙት ነው በሚል ሌላ ርአሰ ጉዳይ ዜ ዜ ዜሙሙ ሥ መንፈሳዊ አገልግሎት ሊያስተምር ይችላል በዚህ ምክንያት ሁሉም መምህራን አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የሸሹት ወቅታዊው ትምህርት ሳይሰጥ ይቀራል ምእመናንም መሠረታዊ አውቀት የሚያገኙበትን ነገረ ፃይማኖትን የሚረዱበትን ትምህርት አያጡ ሲሄዱ በብዙ መልኩ ይጎዳሉ ጠንካራ ትምህርትን የመማር ትእአግሥታቸውም እየሳሳ ይሄፄዳል የዘመኑን ነባራዊ ሁኔታ በመከተል ከበዓላት ባሻገር በሀገሪቱም ሆነ በዓለም ልዩ ልዩ ተፈጥሮአዊ ክስተቶች ማኅበራዊ ቀውሶች ውዝግቦች ይከሰታሉ በምእመናን ፃይማኖትና ምግባር ላይ ተጽፅኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ሁኔታዎች ይፈራረቃሉ አጠራጣሪ የሆኑ የሐሰት ትምህርቶች ፍልስፍናዎች በልዩ ልዩ መንገዶች ወደ ሕዝቡ ጆሮ ይደርሳሉ በዚህ ወቅት መምህራን በንባብና በመረጃ እየቀደሙ በጸሎት እየተመሩ ለወሳኝ ጥያቄዎችና ግርታዎች መልስ ሠጪ የሆኑ ትምህርቶችን ማስተማር ይጠበቅባቸዋል መምህረ መምህራን ኢየሱስ ክርስቶስ በጊዜው ይፈጠሩ ለነበሩ ክስተቶችና ለደቀመዛሙርቱ ጥያቄ ምላሽ ወይም ተያያዥ ትምህርቶችን ይሠጥ ነበር ሉቃ ኞ ሌላው ቀርቶ አርሱ በሰው ልብ ያለውን ያውቅ ነበርና በኅሊናቸው የሚፈጠረውን ግርታም ሆነ ማጉረምረም በማየት ምላሽ የሚሠጥ ትምህርትን ይሠጥ ነበር ይህም መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ጥያቄ ለማያልቅበት ትውልድ ሁሉ ምላሽ ሊሠጥ የሚችለውን መጽሐፍ መንፈሳዊ አገልግሎት ቅዱስ በመጠቀም እንደየሁኔታው ማስተማር እንደሚገባቸው ያስረዳል ለ አለምልሞ መገሠፅ አንድን ሰው ከመገሠፅና መስበክ በፊት ማስተማር ይቀድማል ጌታችን ለኒቆዲሞስ በጥምቀት ዳግመኛ ስለመወለድ አብራርቶ ካስተማረው በኋላ ሲጠራጠር ቢያገኘው አለምልሞ ገሠፀው ሐዋርያትም እንደጌታቸው ትምህርትን አስቀድመው ዘለፋን ያስከትሉ ነበር ሐዋ አንድን ሰው እግዚአብሔርን አንዲፈራ ከመስበክ በፊት ስለ እግዚአብሔር አምላክነት ማስተማር ይቀድማል ቤተ ክርስቲያናችን በሥርዓተ ትምህርቷ ከተግሣፅና ስብከቷ ትምህርቷ የሚያይለው ሰው ፃይማኖቱን ከተማረና ካወቀ ምግባሩ ስለሚቀናና ሕይወቱን ስለሚመረምር ነው የትምህርት ማጣት ግን ከምግባርም አልፎ ፃይማኖትን ያሳጣል ያስክዳልም ወበተኀጥኦ ትምህርት ይበዝጉ መናፍቃን በትምህርት መታጣት መናፍቃን ይበዛሉ እንዲል ፊልክ ምእመናንም ከፃይማኖት የሚወጡት ሳይሰበኩ ቀርተው ሳይሆን ሳይማሩ ቀርተው ነው ባለቤቱም ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቷል ሕዝቤ ያላቸው ምእመናን በኃጢአ ትምህርት በትምህርት እጦት እንደሚጠፉ ተናግሯል ሕይወትን ብቻ የሚመለከት ትምህርት የሚሰጠው ሕዝብ የሚፈለገውን ያህል መንፈሳዊነት ሊገኝበት አይችልም ሳይዘሩ ማጨድ አይቻልምና ለማያውቀው ነገር አንዲታመን መጠበቅ አይቻልም ካልተማሩ አያውቁ ካላወቁ አይጸድቁ አንዲሉ አበው ሳያስተምሩ ደርሶ ምእመናንን መገሠፅ ለመንፈሳዊ ሕይወት አዲስ የሆኑትንና ያልጸኑትን ነፍሳት እንዲሰቀቁ ያደርጋል ውኃ ቀስ ብሎ ሲወርድ የተዘራውን እንደሚያበቅል በኃይል ሲወርድ ደግሞ ጥፋት እንደሚያደርስ ሳያስተምሩ መገሠፅም ውጤቱ ጉዳት ሊሆን ይችላል። አላቸው እንጂ ሕዝቡ ከሚሄድስ ትምህርቴን እነደሚፈልጉት ላድርግላቸው አላለም ዮሐሄጃ መንፈሳዊ ትምህርትም መሰጠት ያለበት አንደቤተክርስቲያን ሥርዓት አንጂ እንደሕዝቡ ፍላጎት አይደለም አንድ መምህር ሕዝቡን ለመሳብ ብሎ መናኛ ነገር እያስተማረ ቢይዛቸው ሊከተሉት ይችሉ ይሆናል ነገር ግን መከተላቸው የሜቆየው መንፈሳዊ ትምህርት ምን እንደሆነ እስኪያውቁ ድረስ ነው በቃና ዘገሊላ በሠርጉ ቤት የታደሙት ሰዎች ጌታችን በኃልዮ ከውኃነት የለወጠውን መልካሙን የወይን ጠጅ በቀመሱ ጊዜ አስቀድሞ ሲጠጡት የነበረውን መናኛ ወይን አእንዳጣጣሉና ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኋላ መናኛውን አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከአሁን አቆይተሃል እንዳሉ አንድ መምህር መናኛ የሆነ ዋዛ ፈዛዛን ሲያስተምራቸው የቆዩ ምእመናን የመንፈሳዊ ትምህርትን ምንነት ሲረዱ የሱን ትምህርት መናኛ ማለታቸው አይቀሬ ነው መንፈሳዊ ብስለታቸው አምብዛም ከሆነ ደግሞ የሚወስዱት እርምጃ ትምህርቱን መናኛ ከማለትም ያለፈ ሊሆን ይችላል ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የላከለት ክታብ በአሕርግጥም በማስተማር ለሚያገለግሉ ሁሉ ስንቅ ነው በእግዚአብሔር ፊት መንፈሳዊ አገልግሎት በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት በመገለጡና በመንግሥቱም አመክርዛለሁ ቃሉን ስበክ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሥሠበት ከዘመን ይመጣልና ነገር ግን ጆሮዎቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ እንደገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ እውነትን ከመስማት ጆሮዎቻቸውን ይመልሳሉ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ መከራን ተቀበል የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ አገልግሎትህን ፈጽም ጢሞፅ መ ተርጉሞ ማስተማር በንባብ ተጠርበው በትርጓሜ የተቀረጹት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ወኢነኀድጎ ዘእንበለ ትርጓሜ ለኩሉ ዘነበብነ የተናገርነውን ሁሉ ያለትርጓሜ አንተወውም ይላሉ በእርግጥም የተራቀቀ የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ ስልት ያለባት እንኳን የአሥራው መጻሕፍት የመጽሐፍ ቅዱስ ይቅርና የአዋልድ መጻሕፍትም ትርጓሜ ያለባት ቤተ ክርስቲያን አለችን በዚህች ቤተ ክርስቲያን ሥር ሆኖ ከምሥጢር የተራቆተ ከንባብ ያላለፈ ትምህርተ ማስተማር የአባይን ልጅ ውኃ ጠማው ያሰኛል ስለዚህ መንፈሳዊው ትምህርት ሊሆን የሚገባው ንባቡን በማብዛት ምሥጢሩን በማሳነስ አይደለም ንባቡን በማሳነስ ምሥጢሩን በማብዛት ነው እንጂ የአንድ ትምህርት ጥቅሙ የሚለካው እጅግ ብዙ ጥቅስ አየጠቀሱ ኃይለ ቃል በማባከን ሳይሆን አንዱን ኃይለ ቃል ዴፌሔቬቨሙመ መመመ መንፈሳዊ አገልግሎት በጥልቀት በማስተማር ነው አባቶቻችን አንዲቱን ጥቅስ ይዘው ሲያመሠጥሩና ሲተረጉሙ እንደኖሩ በመጻሕፍት ተቀምጦ እናገኛለን እንዲያውም የዋኙበት የምሥጢር ማዕበል ራሳቸውን አስደንቋቸው በአንዳንድ የትርጓሜ አንቀጾች አስመ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ዘከመዝ አምሳሊሁ ያመጽእ ብዙኃ ፍካሬ አኮ በብዝኃ ንባብ አላ በኅዳጥ የመንፈስ ቅዱስ ነገሩ እንዲህ ነው ብዙ ትርጓሜን ምሥጢርን ያመጣል በብዙ ንባብ ጥቅስ አይደለም በጥቂት ነው እንጂ ሲሉ እናገኛቸዋለን ስለዚህም ኦርቶዶክሳዊ መምህር ተርጉሞ ማስተማር ይገባዋል አንድ መምህር ማሰብ ያለበት ስለ ረዥም ሰላምታና ምርቃት ስላማረ አለባበስ ስለ ድምፅ አወጣጥ ወዘተ ሳይሆን በትምህርቱ ውስጥ ስላለው ቁምነገርና ከሚሰጠው ትምህርት ምእመናን ስለሚጨብጡት ግንዛቤ ወይም ለየትኛው መንፈሳዊ ሥራ ስለመነሳሳታቸው ነው ትምህርቱ ፍሬ አልባ ሆኖ ላይ ላዩን ያሸበረቀ መምህር ራሱን ከማስናቅና ሲያዩት ይመስሳላሳል ከሚል ትችት ውጪ ምንም አያተርፍም አንደ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ነቢዩ ይህን ስለማን ተናግሮታል ስለራሱ ነው ወይስ ስለሌላ። በአንድ ጊዜ ሁሉንም ትምህርት ለማስተማር አይቻልም ሁሉን በአንዴ ለማስተማር የሚሞክር መምህር ምእመናንን ለጥርጥር ሊዳርግና ብዙ ጥያቄዎችን በኅሊናቸው ሊያስቀምጥ ይችላል እሱ ያወቀውን ሁሉ በአንድ ጊዜ ለመናገር መሞከር የለበትም መምህሩ የደረሰበት እውቀት ለማሳየት ብሎ ከምእመናን የመረዳት ዓቅም በላይ የሆነ ትምህርት ለማስተማር ቢነሣ ትምህርቱ ውጤት አልባ ይሆናል አባት ለሕፃን ልጁ በሚገባው ነገር እንደሚያስረዳው ምአመናንን በትምህርት ወልደው የሚያሳድጉ ምእመናንም ሊረዱት በሚችሉት መንገድ ማስተማር አለባቸው ሊቀ መምህራን ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን ሲያስተምር በሚገባቸው መንገድ ነበር መስማትም በሚችሉበት መጠን እነዚህን በሚመስል በብዙ ምሳሌ ቃሉን ይነግራቸው ነበር» ተብሎ ተጽፏል ወጋህነመሃ ለምኃሳ ፖናሮሙ ቃታሥ ዕላምማታ ይይታ ቃማሜ እንዲል ማርፀ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ባልታደሰ አሮጌ ኅሊናቸው ሊረዱት የማይችሉትን ምስጢር እየነገረም ግራ አያጋባቸውም ነበር «የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም በማለት ተናገሮአል ዮሐጳጂባ ትምህርቱንም ሰዎች ከሚኖሩበት የአኗኗር ዘዬና ከፅለት ተፅለት ተግባራቸው ጋር አስተሳስሮ ያስተምራቸው ነበር ለገበሬው በዘርዕና በአትክልት ሥፍራ ለእረኛው በእንስሳት ለሴቶች በእርሾ ለነጋዴው በገንዘብ እንዲሁም ሁሉም ለው ሊረዳቸው መንፈሳዊ አገልግሎት በሚችሉ ተፈጥሮአዌ እውነታዎች ላይ ምሳሌን እየመሰለ ማስተማሩ ለሰው በሜረዳው ለማስተማርና ትምህርቱን ከሰማዕያነ ዓቅም ጋር ለማጣጣም ነው ቅዱስ ጳውሎስም ለሽማግሌዎች መካክል ግን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን ማለቱ የሰማዕያኑን ዐቅም እንደሚገመግም ያሳያል ቆሮ ከዚህ በተጨማሪ አንድ መምህር የሚያስተምረውን ትምህርት ከሚያስተምራቸው ሰዎች ነባራዊ ሁኔታ ጋር ማገናዘብ ያስፈልገዋል የምእመናንን ኅሊና የሚጎዳ ንግግርና አገላለጽ ቤት ይመታል ይገጥማል እያሉ ተገኘ ብሎ መናገር አይገባም ተስፋ የሚያስቆርጥ ግራ የሚያጋባ ጥያቄ የሚሜፈጥር የሚያጠራጥር ትምህርት ከማስተማር አለማስተማር ይሻላል ምዕመናን አክብሮት ይዞአቸው በዝምታ ስለሰሙ አይታዘቡም ማለት አይደለም ስለዚህ መምህሩ ምእመናን የዛሬው መምህር ሲዘላብድ አመሸ ሊሉ የሚችሉ መሆናቸውን መገመት አለበት አስቲ ጥቂት ምሳሌዎችን እናንሣ በአንድ ጉባኤ ላይ አንድ መምህር ስለ መካንነት እያነሣ ሲያስተምር ልጅ ባትወልዱስ ምን ችግር አለው በተወደደ ኑርሮ ዓይኔ በዓይኔ ካላየሁ አትበሉ መስታወት አለ አይደል እያለ ይናገር ነበር ይህ ዓይነቱ ትምህርት ከቤተ ክርስቲያን የተገኘ ሳይሆን የመምህሩ አስተያየት ነው ይህ ትምህርት የሚያርፍበት ቦታ ግን የት እንደሆነ አይታወቅም በዚህ ንግግር የሚቆስል ልብ ግን ይኖራል በዚያ ላይ ልጆች የአግዚአብሔር ሥጦታዎች ዴ። ሠ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያዎች ከሆኑ ከመጽሐፍ ቅዱስና ከኣዋልድ መጻሕፍትና ከትውፊት ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ ነው ለመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተዘጋጁ የትርጓሜ መጻሕፍት አሉ እነዚህን ሊያካትት የማይፈቅድ መምህር ኦርቶዶክሳዌ ሰባኪ ነው ለማሰት ያስቸግራል ክርስቲያናችን ሰፍራ ቁጥራ በቀኖና የለየቻቸውና አነዚህን ቤተ የምትቀበላቸው ሰማኒያ አንድ መጻሕፍት አሏት መጻሕፍት በሙሉ አምነት ተጠቅሞ ማስተማር የመምህራን ሥራ ነው በመጻሕፍቱ አምናለሁ አያለ ሲጠቅሳቸው የማይፈልግ መምህር በቃሉም ባይሆን በተግባር አየካዳቸው ነው ከመጽሐፍ ቅዱስ የተገኙ አዋልድ መጻሐፍትንም መጠቀም ይገባል ቅዱስ ጳውሉስ ለጢሞቴዎስ የአእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማጽናት በጽድቅም ላለው ምክር ሁሉ ይጠቅማል ብሎታል ይህም አዋልድ መጻሕፍት ለትምህርት ለተግሣጽ አንደሚጠቅሙ የሚያስረዳ ነው ዘጢሞካ የቅዱሳን ገድላትና ተአምራት እየጠላ ቅዱሳንን አምናለሁ ማለት አይቻልም አባ ጽጌ ድንግል ለእመቤታችን በደረሰው ምስጋናው አወድጓለሁ የሚል ክርስቲያናዊውን ተአምርሽን የማይወድ አይሁዳዊና የሐሰተኛው አስጢፋ ውጤት ነው እአንጂ ብሏል በሰይብል አፈቅረኪ ወኢያፈቅር ተአምረኪ ክርስቲያናዊ ኢ ጨመ መንፈሳዊ አገልግሎት መመ መጨ ክርስቱን ውእቱ ዳዕሙ አይሁዳዊ ወሠርፀ እስጢፋ ሐሳዊ እን«ል ማኅሌተ ጽጌ ተብሎ ይታመናል አባቶች ይላሉ ምናልባት የሚሉ ቃላትን የሚጠቀም መምህር ከእምነት ጋር እያስተማረ ነው ማለት አይቻልም በሕይወቱ የተረዳውን የሚያስተምር መምህር ግን ሌሎችን እርሱ ያየውን እንዲያዩ ሊስባቸውና ሊያጓዓቸው ይችላል መንፈሳዊ ትምህርትን ለማስተማር እውቀት ብቻ አይበቃም ቅዱሳን ሐዋርያት የስማነውን እንናገራለን ያየነውን እንመሰከራለን እሉ አስተምረዋል እንደነርሱ የጌታችንን ትምህርት በቃል ሰብኦዊ በሰው ቃል ሲነገር ባይሰማ የአጃን ተአምራት ማየት ባይቻለውም አንድ መምህር በእምነት መነጽር የተረዳውን ማስተማር አለበት ከሚናገረው ምሥጢርም እሉ በአፍአ ውጪ መሆን የለበትም አዚህ ጋር ሊታይ የሚችለው ነገር ብዙ ቅዱሳን ባሉባት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የማያምኑ ሰዎችን አብነት አድርጎ መጥቀስ እንደማይገባ ነው እንደ ደመና የከበቡ ምስክሮች በዙሪያችን አሉልን ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረ ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ተጋድሎን የፈጸመ ምሳሌ የሚሆን ሕይወት ያላቸው ብዙ ቅዱሳን አሏት መናፍቃንና አሕዛብ በብዙ ጉዳዮች መልካም ምገባር ሊኖራቸው ቢችል አንኳን ዛይማኖት የሌለውን ምግባራቸውን እየጠቀስ ምእመናንን ማስተማር ሰመምህሩ አይገባውም ለምሳሌ አረማዊያን ሴቶች አለባበሳቸው ሥርዓት ያሳው ነው ሊባል ይችላል ነገር ግን ምእመናን ስለ ተገቢው ኦለባበስ ጫሙመሙመሙሙ ለማስተማር ቅዱሳን አበውና እማትን እናቶችን ምሳሌ ማድረግ ይቻላል እንጂ አረማያንን እዩ ሊባል አይገባውም ቅዱስ ጳውሎስ ስለ አለባበስ ሲናገር ዳሩ ግን ማንም ሊከራከር ቢፈቅድ እኛ ወይም የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት አንዲህ ያለ ልማድ የለንም ብሎአል እንጂ የሌሎችን አለባበስ አልጠቀሰም ጳቆዋሮይጳ። በእርግጥም ስለአለባበስ ለሚከራከሩ ቤተ ክርስቲያናችን ሀገራችንም አንዲህ ያለ ልማድ የላትም በማለት ማስተማር ይቻላል እንጂ አሕዛብን በምንም አብነት ማድረግ አይገባም አለባበስን ለምሳሌነት አነሣን እንጂ ከዚህ በላይ በብዙ ጉዳዮች ላይ ምእመናን ግራ እስከሚጋቡ ድረስ መናፍቃንን አርአያ ተደርገው የሚጠቀሱበት ጊዜ አለ ማጠቃለያ በቤተ ክርስቲያናችን ስብከተ ወንጌል በዐውደ ምሕረት ሰዓት ተይዞለት መካሔድ ከጀመረ ዓመታት አሳልፎአል እንዲሁም ጥልቀት ያለው ትምህርት የሚሠጥባቸው እንደ መንፈሳዊ ኮሌጆች ስንበት ትምህርት ቤቶች እና ጊቢ ጉባኤያት ለምእመናን ክፍት ሆነዋል ሆኖም ምእመናን ስለ ሃይማኖታቸው ያላቸው ግንዛቤ አሁንም በአስጊ ደረጃ ላይ ይገኛል በሐሰት ትምህርቶች ተታልለው ወደ ክህደት የሚነዱ ነፍሳት ቁጥርም እጅግ ብዙ ነው ስለዚህም የመማር ማስተማሩ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት አሁን ከተሠጠው ስፍራ የበለጠ ስፍራ ሲሰጠው ግድ ይላል ሰለዚህም የሚከተሉት ነጥቦች ትኩረት የሚሹ ናቸው መመመ ምእመናን ሊረዱት በሚችሉት ቀላል መንገድ ማስተማር ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እንኳን ኢትዮጵያውያንን ዓለምን ልትማርክ የምትችልበት ውበት ያላት በነገረ ክርስቶስና በትምህርተ ወንጌል የተራቀቀች ቅዱሳት መጻሕፍት ከግራ ከቀኝዋ እንደ ወንዝ የሚፈስሱባት ናት አንድ ሊቅ አፍላገ ግዮን ወጤግሮስ ይውኅዙ በወንጌል ሐዲስ አምየማና ወእምጸጋማ ኤፍራጥስ ኢትዮጵያ ሀገረ ክርስቶስ በግዮንና በጤግሮስ በኤፍራጥስ ወንዞች የሚመሰሉት አራቱ ወንጌላት ከቀኝዋ ወደ ግራዋ ይፈስሳሉ ኢትዮጵያ የክርስቶስ ሀገር ናት ያሉት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያለው የነገረ ፃይማኖት ጥበብ ከአእምሮአቸው በላይ ቢሆንባቸው ነበር ይህንን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብትና ጥበብ ግን ለዚህ ትውልድ በሚረዳው እና በሚገባው መንገድ ማስተዋወቅ ባለመቻሉ ቤተ ክርስቲያኒቱን ብዙዎች ሳያውቋት እንዲቀሩ አድርጓል ከፍ ሲልም ከጉልላትዋ እስከ መሠረትዋ ከዜማዋ እስከ መጻሕፍትዋ በነገረ ክርስቶስ የተሞላችና ስለ አምላክ ሰው መሆን የተራቀቀ የምሥጢረ ተዋሕዶ ትምህርት የሚሜሰጥባትን ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን አታውቀውም ብለው እስከመዝለፍ የሚደርሱ ሰዎችም ሊፈጠሩ ችለዋል በዚህ ትችት እሰጥ አገባ ውስጥ ከመግባት ቤተ ክርስቲያኒቱ ያላትን የተራቀቀ ትምህርት ለምእመናን ማሳየት የመምህራን ፈንታ ነው የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓተ አምልኮ ምንነት ምአኦመናን ለመረዳት እንዲችሉ የግእዝ ትምህርት ለሁሉ እንዲዳረስ ማድረግ መው ክክይዊ መንፈሳዊ አገልግሎች አስፈላጊ ነው ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ባለሰሙትስ እንዴት ያምናሉ የሚለውን ቃለ ሐዋርያ መጥቀስ አይቻለንም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሁለት ዓይነት መምህር አለ ይላሉ አንደኛው ለሕዝቡ የሚያሳውቅ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ማወቁን የሚያሳውቅ ነው በእርግጥም መምህራን አዋቂ የሚሰኙት ሌላውን ካለማወቅ ነጻ ሲያወጡ ብቻ ነው ትሑት ባሪያዬ በአውቀቱ ብዙዎችን ያጸድቃል ተብሎ ለጌታችን አንደተነገረ ኢሳ ስለዚህ መምህራን በዕውቀታቸው ሳይታበዩ ምአመናን በሚረዱት መንገድ የማስተማር ሓላፊነት አለባቸው ዘመኑን የዋጀ የማስተማር መንገድ መከተል ቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ ትምህርትዋን በየዘመነ የምትለዋውጥ አይደለችም የትምህርት አሰጣጥዋ ግን እንደየዘመኑ ሁኔታ መሆን ይኖርበታል በዚህ ዘመን አጭጫር ርአሰ ጉዳዮችን የተከተሉ ትምህርቶች መሥጠት አስፈላጊ ነው ጭብጥ የሌለውና ውጤቱ ከንፈር ማስመጠጥ ብቻ የሆነ ትምህርት መሥጠት ዘላቂ መፍትሔ አያስገኝም ሕዝቡ ስለ ሃይማኖቱ በእርግጠኝነት ለመመስከር የሚችልበት የተብራራና ግልፅ የሆነ ለሁሉም ሰው የሚረዳ የትምህርት መንገድ መከተል የግድ ይላል ከዚህ ባሻገር ምእመናን በማይረሷቸው ምሳሌዎች ከማዝናናት ይልቅ አይረሴነት ባላቸው ጽንሰ ሃሳቦች በቃል ሊጠኑ በሚችሉ ሃሳቦች ኦርቶዶክሳዊውን ትምህርተ ሃይማኖት ማስጨበጥ የመምህራን ድርሻ ነው አንድ ሳይንቲስት እንደተናገረው ንፈሳዊ አገልግሎች አንድ መምህር የሚያምንበትን ነገር ለትንሸ ትልቁ በሚገባ መንገድ ማስረዳት ካልቻለ ለራሱም አልገባውም ማለት ነው ሃይማኖታችን እንደ ሌሎች በጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ላይ አልተመሠረተችም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንጂ።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF


Download options | Convert to Pdf | Advertise on dirzon

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact